Know Your Rights when Interacting with ICE in the DMV

تعرف على حقوقك عند الاحتكاك بإدارة الهجرة والجمارك (ICE) في منطقة العاصمة واشنطن الكبرى (DMV)

了解在DMV与ICE接触时的权利

Connaissez vos droits lorsque vous êtes en contact avec l'ICE dans la région du DMV

በDMV (ዲ.ሲ.፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ) ክልል፣ ሰዎች በየዕለቱ የህግ የአስተዳደር ድንበሮችን እያቋረጡ በሚኖሩበት ሁኔታ፣ የኢሚግሬሽን ሕግ አስከባሪ እንደ ክልል የሚሠራ ኃይል ይሆናል። በዚህ ክልል የሚኖሩ ቤተሰቦች ብዙ ጊዜ በአንድ የአስተዳደር ክልል ይኖራሉ፣ በሌላ ክልል ይሠራሉ፣ እንዲሁም በስቴት እና በዲስትሪክቱ ድንበሮች ተሻግረው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና የሕዝብ አገልግሎቶችን ይጠቀማሉ።

ነገር ግን እነዚህን ድንበሮች ሲያቋርጡ መብቶችዎ አይለወጡም።

በ ICE ከተለዩ ወይም ከተቆሙ ምን ማድረግ እንዳለብዎ

የአሜሪካ ዜጋ ካልሆኑ እና በፖሊስ ወይም በ ICE እንዲቆሙ ከተደረጉ ወይም ከተጠየቁ የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት፡-

  • ዝምታን መምረጥ (ምንም አለመናገር)።
  • መረጋጋት።
  • ፍተሻ እንዲደረግ ሲጠየቁ “አይሆንም” ማለት።
  • በጭራሽ የሐሰት ሰነዶችን አያሳዩ።
  • የአሜሪካ ዜጋ ነኝ በማለት በጭራሽ አይዋሹ።

ስለሚከተሉት ጉዳዮች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ የመስጠት ግዴታ የለብዎትም፡-

  • ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታዎ።
  • የት እንደተወለዱ።
  • ወደ ሀገር እንዴት እንደገቡ።

በቤትዎ ውስጥ

ICE ወይም ፖሊስ ወደ ቤትዎ ከመጡ፡-

  • ይረጋጉ
  • በሩን አይክፈቱ።
  • ወደ ቤትዎ አይጋብዟቸው።
  • እርስዎን ለማሰር የሚያስችል የፍርድ ቤት ማዘዣ ካላቸው፣ በበሩ ቀዳዳ እንዲያሳዩዎት ወይም በበሩ ስር እንዲያሾልኩት ይጠይቋቸው።
    • የ ICE ማዘዣ (ፎርም 1-200) ወደ ቤትዎ ለመግባት ፈቃድ አይሰጣቸውም።
    • በዳኛ የተፈረመ የወንጀል የእስር ማዘዣ ግን ወደ ቤትዎ እንዲገቡ ሊፈቅድላቸው ይችላል።
  • ዝም የማለት መብት አልዎት
  • አይዋሹ።
    • በሐሰት የአሜሪካ ዜጋ ነኝ ብለው በጭራሽ አይናገሩ።
  • ማንኛውንም ዓይነት የሐሰት ሰነድ አያሳዩ።
    • ይህም የሐሰት የመንጃ ፈቃድ፣ የሶሻል ሴኩሪቲ ካርድ ወይም የኢሚግሬሽን ሰነዶችን ያጠቃልላል።
A black‑and‑white photo of the front of a suburban house with an orange geometric background and a stylized ICE badge illustration on the right.

በመኪና ውስጥ

በሚያሽከረክሩበት ወቅት ወይም ተሳፋሪ ሆነው እንዲቆሙ ከተደረጉ፡-

  • ደህንነትን በጠበቀ መንገድ እና በፍጥነት መኪናውን ወደ ዳር ያቁሙ።
  • ሞተሩን ያጥፉ፣ የውስጥ መብራቱን ያብሩ እና መስኮቱን ይክፈቱ።
  • ሲጠየቁ ለፖሊስ (1) የመንጃ ፈቃድዎን፣ (2) ሊብሬ (የምዝገባ ሰነድ)፣ (3) የኢንሹራንስ ማረጋገጫ ይስጡ።
    • ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ከሌለዎት የሐሰት ሰነዶችን አይስጡ።
  • ለፖሊሱ መኪናዎን እንዲፈትሽ ፈቃድ አይስጡ።
    • “አይሆንም” ካሉ በኋላም መኪናዎን ቢፈትሹ፣ ተቃውሞ አያድርጉ (አይጋፈጡ)።
  • ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታዎ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ አይስጡ።
    • ፖሊስ ከሆኑ ስማቸውንና የባጅ ቁጥራቸውን ጠይቀው መጻፍ አለብዎት።
    • ICE ከሆኑ እና ግሪን ካርድ ወይም የሁኔታ ማረጋገጫ ከጠየቁዎት፣ ካለዎት ለባለስልጣኑ ማሳየት አለብዎት።
A black‑and‑white photo showing a uniformed officer interacting with someone in a car, with an orange geometric background and a stylized ICE badge illustration on the right.

በሥራ ቦታ

ICE ወደ ሥራ ቦታዎ ከመጣ፡-

  • ይረጋጉ
  • አይሩጡ።
  • ወደ ህንጻው የግል ቦታ ይሂዱ።
    • ለሕዝብ ክፍት ያልሆነ የሥራ ቦታ ክፍል (ለምሳሌ፦ የምግብ ቤት ኩሽና) ለመግባት ICE ከዳኛ የተሰጠ ማዘዣ ወይም የአሠሪዎ ፈቃድ ያስፈልገዋል።
  • ዝምታን መምረጥ (ምንም አለመናገር)።
    • ለ ICE መታወቂያዎን፣ የሥራ ፈቃድዎን ወይም ማንኛውንም ወረቀት የመስጠት ግዴታ የለብዎትም።
    • የሚሰጧቸው ማናቸውም መረጃዎች በእርስዎ ላይ ማስረጃ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ።
A black‑and‑white aerial view of a mostly empty parking lot, layered over an orange geometric shape, with a stylized ICE badge illustration on the right.

በ ICE በቁጥጥር ስር ከዋሉ ምን ማድረግ እንዳለብዎ

  • መረጋጋት።
  • ዝምታን መምረጥ (ምንም አለመናገር)።
  • ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታዎ ከጠበቃዎ ጋር እንጂ ከማንም ጋር አይወያዩ።
  • ያልተረዱት ነገር ላይ አይፈርሙ።
  • አስተርጓሚ እፈልጋለሁ ብለው ይናገሩ።

በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ፡-

በፖሊስ ከተያዙ

  • መክፈል ባይችሉም እንኳ ጠበቃ የማግኘት መብት አለዎት።
  • የስልክ ጥሪ የማድረግ መብት አለዎት።
  • ከጠበቃ ጋር ካልተነጋገሩ በስተቀር ሁሉም የስልክ ጥሪዎች ክትትልና የተቀረጹ መሆናቸውን ያስታውሱ።
An orange, sketched illustration of a five‑pointed sheriff‑style star badge on a light background.

በ ICE ከታሰሩ፡-

በICE ከተያዙ

  • የራስዎን ጠበቃ የመቅጠር መብት አለዎት።
  • መታሰርዎን ለመንገር የሀገርዎን ቆንስላ የማነጋገር መብት አለዎት።
  • እርስዎን ለማግኘት እንዲችሉ የእርስዎን የኢሚግሬሽን ቁጥር ወይም “A-number” (ባለ 9 አሃዝ) ለቤተሰብዎ ይስጡ።
An orange, stylized illustration of a U.S. ICE officer badge on a light background.

በዲ.ሲ.፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ ውስጥ ቁጥጥር ስር ስለማዋል፣ ስለማሰር እና ከአገር ስለማባረር በተመለከተ የሕግ ድጋፍ እና መረጃዎች፦

እርስዎ ወይም ወዳጅዎ ለእስር፣ ከአገር ለመባረር ወይም ለማንኛውም ውስብስብ የኢሚግሬሽን ጒዳይ ከተጋለጡ እነዚህ ቡድኖች ነጻ ወይም አነስተኛ ዋጋ ያለው የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ይሰጣሉ።

የኢሚግሬሽን ጠበቆች መረብ (Immigration Advocates Network): www.immigrationadvocates.org

የአሜሪካ የኢሚግሬሽን ጠበቆች ማህበር (American Immigration Lawyers Association)፦ www.ailalawyer.com

ነፃ የህግ አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር (የፍትህ መምሪያ)፡- https://www.justice.gov/eoir/file/probonofulllist/dl

የጥገኝነት ጥያቄ ተሟጋቾች፡- https://asaptogether.org/es/

ICE – በቁጥጥር ስር የዋለ ሰው የመስመር ላይ ጠቋሚ አመልካች ስርዓት:- https://locator.ice.gov/odls/#/search

ሂዩማን ራይትስ ፈርስት (Human Rights First): https://readynow.app.link/download

የዲሲ የጋራ መረዳጃ የስልክ መስመር (DC Mutual Aid Hotline)፦ 202-335-1183 https://www.dcmigrantmutualaid.org/hotline

Related Content


News & Commentary
Jan 20, 2026
Immigrants are welcome here

What Trump’s Immigration Policies Mean for Families Across the DMV

Since the start of President Trump’s second term, immigrant communities across the District of Columbia, Maryland, and Virginia have been living with an immigration agenda once again defined by fear, intimidation, and aggressive federal enforcement. While these policies are often most visible in Washington, D.C., their consequences do not stop at the District line.